ሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማምቷል

ወጣቱ ግብ ጠባቂ ዳግም ተፈራ ለሀዋሳ ከተማ ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ሰልጥኖ ካለፈ በኃላ 2008 ላይ የሀዋሳን ከ17 ዓመት በታች ቡድን ተቀላቅሎ የክለብ ህይወት የጀመረው ግብ ጠባቂው ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ ለሀዋሳ ከ20 ዓመት በታች ቡድንም ተጫውቶ ከሁለቱም ቡድኖች ጋር የሊግ ዋንጫ ከማሳካቱ ባሻገር በ2009 ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂም ተብሎ ተሸልሟል፡፡ በአሰልጣኝ አጥናፍ ዓለሙ አማካኝነት በወቅቱ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንም ተጠርቶ መጫወት ችሏል፡፡

2010 ለሀዋሳ ዋናው ቡድን ካደገ በኃላ ብዙም የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ 2011 ለዲላ ከተማ ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ደግሞ በደቡብ ፖሊስ መልካም የውድድር ጊዜን አሳልፎ በድጋሚ ወደ ልጅነት ክለቡ ሀዋሳ ከተማ በመመለስ ለሁለት ዓመት ኮንትራት ተስማምቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ