ወልቂጤ ከተማ አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ወልቂጤ ከተማ የአጥቂ መስመር ተሰላፊው አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል።

የቀድሞው የጅማ አባ ቡና እና ኢትዮጵያ ወጣት ቡድን አጥቂ አባ ቡናን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደጉ ወሳኝ ሚና የተጫወተ ሲሆን በሊጉ ያሳየውን ጥሩ እንቅስቃሴ ተከትሎ በ2009 ክረምት ነበር ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው። በፈረሰኞቹ የተጠበቀውን ያህል የተሰላፊነት እድል ያላገኘው አሜ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር በመለያየት ወልቂጤን ለመቀላቀል ተስማምቷል። ጫላ ተሺታን በማጣታቸው የተፈጠረውን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎም ይጠበቃል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ክስተት የነበረው ረመዳን የሱፍ ጨምሮ ስድስት ተጫዋቾች ለማስፈረም የተስማሙት ወልቂጤዎች ቀደም ብለው የበርካታ ነባር ተጫዋቾች ውልም ማራዘማቸው ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ