ሠራተኞቹ የመስመር ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ

አንዱልራህማን ሙባረክ ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ተስማማ።

ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ፋሲል ከነማ ከተቀላቀለ በኃላ በ2008 ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ እና በሊጉ የተረጋጋ ዓመት እንዲያሳልፍ ጉልህ ድርሻ ካደረጉት ተጫዋቾች በግንባር ቀደም የሚጠቀሰው ይህ ፈጣን የመስመር ተጫዋች ባለፈው ዓመትም በተወሰኑ ጨዋታዎች ቡድኑ ማገልገሉ ይታወሳል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት የዋልያዎቹ ማልያ የለበሰው አብዱልራህማን ዛሬ ጠዋት ስምምነት የፈፀመ ሲሆን የአጥቂ አማራጮቹን ለማስፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ለሚገኘው ወልቂጤ ጥሩ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!