የደም ልገሳው በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር ጋር በመሆን ያዘጋጁት የደም ልገሳ መርሐግብር በተለያዩ ከተሞች በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።
የቀድሞ እና አሁን በመጫወት ላይ የሚገኙ እግር ኳስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተሳተፉበት በዛሬው የደም ልገሳ መርሐግብር በተመረጡ ዘጠኝ ከተሞች በሚገኙ የደም ባንኮች በመሄድ በተሳካ ሁኔታ እንደተካሄደ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። በድሬዳዋ የሚገኘው ስፖርት ለሰላም ማኀበር ከድሬደዋ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ጋር በመሆን የደም ልገሳ አድርገዋል።

በአንድ ሰው ደም የሦስት ሰው ህይወት ማትረፍ እንደሚቻል በሚታመንበት በዚህ በጎ ተግባር የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኀበር እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማኀበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በጋራ በመሆን ያደረጉ መልካም ሥራ አድናቆት የሚቸረው እና በቀጣይ መሰል የሆኑ ድጋፎች ይቀጥሉ መልክታችን ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!