‘አወዛጋቢው ሕግ’ ገለፃ ተደረገበት

“የባላጋራ ቡድን ተጫዋችን ለረጅም ጊዜ መከታተል፣ አብሮ መሮጥ እና አጠገቡ መቆም ክልክል ነው” የሚለው ሕግ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮች በቀጣይ ዓመት የሚጀመሩበትን መንገድ አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ አዘጋጅቶ ለክለቦች እያቀረበ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ የተዘጋጀውን መነሻ ሰነድ ለወንዶች ፕሪምየር፣ ከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ክለቦች ማቅረቡ ይታወሳል። በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ ተወካዮች ለብቻቸው ጥሪ ተደርጎላቸው ሰነዱ ቀርቦላቸዋል።

31 ገፆችን ያየዘው ይህ መነሻ ሰነድ ከተለያዩ ሀገራት በተሞክሮነት የተወሰዱ ሕግጋት እና ምክረ ሀሳቦች የሰፈሩበት ቢሆንም እንደ ሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የተወሰዱ መዘርዝሮች በውስጡ እንዳሉት ተገልጿል። እና በዚህ ሰነድ ላይ የሰፈረው ” የባላጋራ ቡድን ተጫዋችን ለረጅም ጊዜ መከታተል፣ አብሮ መሮጥ እና አጠገቡ መቆም ክልክል ነው” የሚለው ምክረ ሃሳብ በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሮ ሲያነጋግር ቆይቷል። ታዲያ ይህንን አነጋጋሪ ነጥብ አስመልክቶ በዛሬው መርሐ-ግብር ላይ የፌዴሬሽኑ የሴቶች ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ጌታቸው የማነብርሃን ገለፃ አድርገዋል።

“ይህ ነጥብ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። ግን ግልፅ መሆን ያለበት ነገር ህጉ በፊፋ ህግ ላይ መቀመጡ ነው። ዓለም ላይ የሚገኙ የእግርኳስ ፌዴሬሽኖች የበላይ የሆነው ፊፋ በቅርቡ ያወጣው ሕግ አለ። እዚህ ሕግ ላይ አሁን የተነሳው ነጥብ በግልፅ ተቀምጧል። ስለዚህ እኛም ነጥቡን ከዛ ነው የወሰድነው።” ብለዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!