በአንድ ሰፈር ተወልደው ያደጉት ሁለቱ የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች አቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንን በኢትዮጵያ ቡና ውላቸውን ለማራዘም ተስማሙ፡፡
በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 2008 ላይ ድንቅ ጥምረትን ያሳዩት ሁለቱ የአንድ ሰፈር አብሮ አደግ ጓደኛሞች 2009 ላይ የሐረር ሲቲን ወጣት ቡድን ለቀው ሁለቱም ወደ ቡናማዎቹ ቤት አምርተው አራት ዓመታትን በመጫወት አሳልፈዋል። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ እምብዛም ባልተለመደ ሁኔታ ለአምስት ተጨማሪ ዓመታት (እስከ 2017) በክለቡ ለመቆየት ተስማምተዋል።
በተለይ አጥቂው አቡበከር ነስሩ ያለፉትን አራት ዓመታት ለኢትዮጵያ ቡና ውጤታማነት የራሱን ድርሻ ያበረከተ ሲሆን ከበርካታ ክለቦች ጋር ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ያመራል ቢባልም ምርጫውን ዳግም ኢትዮጵያ ቡና አድርጓል፡፡
ሌላኛው የመስመር አጥቂው ሚኪያስ መኮንን ለተጨማሪ አመት በክለቡ ለመቆየት የተስማማ ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ ተጫዋቹ ከ2010 እስከ 2011 የተቀዛቀዘ ቆይታ በክለቡ ቢኖረውም ዘንድሮ በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ስር ሊጉ እስከተቋረጠበት ወቅት ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ቡናዎች በቅርቡ ግብ ጠባቂው አቤል ማሞን ከመከላከያ ተከላካዩን ዘካሪያስ ቱጂን ከለገጣፎ ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!