ፀጋዬ አበራ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡
ከአርባምንጭ ከተማ የታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ድረስ በአዞዎቹ ቤት የፕሪምየር ሊግ ቆይታን ካደረገ በኃላ 2011 መስከረም ወር ላይ ወደ ጦና ንቦቹ አምርቶ ሁለት የውድድር ዓመታትን በክለቡ አሳልፏል፡፡ በክለቡ ቆይታው ከሚታወቅበት የመስመር አጥቂነቱ ባሻገር በቀኝ መስመር ተከላካይነት ያገለገለ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ዛሬ ከሰምምነት ደርሷል፡፡
ወላይታ ድቻ በድምሩ የአምስት ነባሮችን ውል ያራዘመ ሲሆን የዛሬውን ፈራሚ ሽመክት ጉግሳን ጨምሮ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!