ሀዋሳ ከተማ የእገዳ ውሳኔ ተላለፈበት

በቀድሞ ተጫዋቹ ገብረመስቀል ዱባለ በቀረበበት ክስ የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ አላደረገም በሚል ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ማንኛውም አገልግሎት ከፈፀዴሬሽኑ እንዳያገኝ ታግዷል።

በ2010 በጨዋታ ላይ እያለ የጉልበት ጉዳት ያጋጠመው ገብረመስቀል ዱባለ አንድ ዓመት ቀሪ የኮንትራት ዘመን እያለው በ2011 ክለቡ መቀነሱን ተከትሎ ቅሬታውን ወደ ፌዴሬሽኑ በመውሰድ መክሰሱ ይታወቃል። ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴም ክለቡ ተጫዋቹን መቀነስ እንደማይችል እና ኮንትራቱን እንዲያከብር ብይን ሰጥቶ ነበር። ሆኖም የሀዋሳ ከተማም ውሳኔው ተገቢ አይደለም በማለት ይግባኝ በመጠየቁ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሀዋሳን ይግባኝ ተመልክቶ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ በ2011 ያልተከፈለው የአንድ ዓመት ደሞዙ እንዲከፍል ውሳኔ አሳልፏል። በሁለቱም የፍትህ አካላት የተላለፈበትን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ የተወሰነበትን ውሳኔ ሳይወስን በመቆየቱ በዛሬው ዕለት ውሳኔውን ተግባራዊ እስኪያደርግ ድረስ ከፌዴሬሽኑ ማንኛውንም አገልግሎት እንዳያገኝ ታግዷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!