ሀዋሳ ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማማ

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ኤፍሬም ዘካሪያስ ወደ ሀዋሳ ከተማ በድጋሚ ለመመለስ ተስማማ፡፡

ከመተሐራ ከተገኘ በኃላ በኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ሰጪን እንቅስቃሴን ካደረገ በኋላ በ2008 ወደ ሀዋሳ ከተማ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አማካኝነት ተቀላቅሎ ለሁለት ዓመታት መጫወት የቻለ ሲሆን ወደ አዳማ ከተማም አምርቶ የሁለት ዓመት ቆይታን በማድረግ ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በወልቂጤ ከተማ ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ዘንድሮ አሳልፏል። ተጫዋቹ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ከሳምንታት በፊት ውሉን ለማራዘም ቢስማማም ከሦስት ዓመታት በኋላ የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ዛሬ ከስምምነት ደርሷል። በዚህም ደስተኛ መሆኑን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

ሀዋሳ ከተማ ከኤፍሬም ዘካሪያስ በፊት ሶሆሆ ሜንሳ፣ ዘነበ ከድር፣ ጋብሬል አህመድ እና ዳግም ተፈራን ለማስፈረም ሲስማማ የበርካታ ነባር ተጫዋቾችን ውልም ለማራዘም መስማማቱ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!