በቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ዓመት ቆይታ ያደረገው እና በቅርቡ ወደ ወልቂጤ ከተማ ለመመምራት የተስማማው አሜ መሐመድ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ይናገራል።
በጅማ አባ ቡና ቀሪ አንድ ዓመት ኮንትራት ቢኖረውም የውል ማፍረሻ አንድ ሚሊዮን ብር በመክፈል በ2010 ወደ ፈረሰኞቹ ቤት ማምራቱ ይታወቃል። በቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስቱን ዓመት ካገለገለ በኃላ በቅርቡ ወደ ወልቂጤ ማምራቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ሶከር ኢትዮጵያ አሜ መሐመድን አግኝታ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስለነበረው ቆይታ እና ስለለቀበት ምክንያት እንዲሁም ከአዲሱ ክለቡ ወልቂጤ ከተማ ጋር ስለሚያስበው ቆይታ ይሄን ነግሮናል።
” በቅዱስ ጊዮርጊስ እኔ በግሌ ጥሩ ጊዜ አሳልፌለው ብዬ አስባለሁ፤ ያው አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩም በቅዱስጊዮርጊስ ደስተኛ ሆኜ ነበርኩ። ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት የነበረኝ ቢሆንም ክለቡ አዳዲስ ተጫዋች በማምጣቱ ከአመራሮች ጋር ተነጋግሬ በውሰት ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቻለው። ወደ ወልቂጤ ያመራሁት በቂ የመጫወት እድል እንደማገኝ በማመን ነው። ራሴንም በሁሉም መንገድ አዘጋጅቼ በወልቂጤ የተሳካ ዓመት አሳልፋለው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።” ብሏል።
ፈጣኑ አጥቂ አሜ መሐመድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ተስፋ ቡድን የእግርኳስ ጅማሬውን በማድረግ በጅማ አባ ቡና የተሳካ የውድድር ዓመት በማሳለፍ በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና በዋናው ብሔራዊ ቡድን መጫወቱ ይታወቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!