ባሳለፍው ዓመት የክረምት የዝውውር መስኮት የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅለው የነበሩት ሁለት ማሊያዊ ተጫዋቾች ከክለቡ ጋር መለያየታቸው ተሰምቷል።
በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት የጣና ሞገዶቹ በተሰረዘው የውድድር ዘመን ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበረ ይታወሳል። ታዲያ በዚህ ስብስብ ውስጥ የነበሩት ማሊያዊ ዜግነት ያላቸው አዳማ ሲሶኮ እና ማማዱ ሲዲቤ በግላቸው ለቡድኑ ጥንካሬ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ድንቅ ነበር። ነገር ግን ተጫዋቾቹ ከቡድኑ ጋር ያላቸው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ ጋር በይፋ መለያየታቸው የተጫዋቾቹ ህጋዊ ወኪል አቶ ኤርሚያስ አሽኔ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ክለቡም ስለመለያየታቸው ለድረ-ገፃችን ማረጋገጫ ሰጥቷል።
1 ሜትር ከ86 ሴንቲሜትር የሚረዝመው ሲሶኮ እና ግዙፉ የቀድሞው ራቻድ ቤርኖሲ የአጥቂ መስመር ተጫዋች ሲዲቤ በጅማ አባጅፋር ቆይታ አድርገው ወደ ባህር ዳር መምጣታቸው አይዘነጋም። በቀጣይ የተጫዋቾቹ ማረፊያ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!