“ተጫዋቹ ስለቸኮለ ነው እንጂ ተስማምተን ነበር” አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ – የሀዋሳ ከተማ ሥራ አስኪያጅ

ከትናንት በስቲያ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግድ ውሳኔ የተላለፈበት ሀዋሳ ከተማ የተነሳበትን ቅሬታ ለመፍታት መዘጋጀቱን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ ተናግረዋል፡፡

ገብረመስቀል 2011 በጉልበቱ ላይ ጉዳት በማስተናገዱ ባለፈው ዓመት በክለቡ የተቀነሰ ሲሆን ተጫዋቹ የተቀነስኩበት መንገድ አግባብ አይደለም በክለቡ የአንድ ዓመት ውል አለኝ በማለት ተጫዋቹ ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሽኑ ወስዶ የክስ ደብዳቤን በማስገባቱ ፌዴሬሽኑ ከአንድ ሁለት ጊዜ ለሀዋሳ ይከፈለው በማለት ውሳኔን ቢያስተላልፍም ክለቡ ዝምታን መመርጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለተጫዋቾቹ የአንድ ዓመት ደመወዙን እንዲከፍል ክለቡ ላይ እግድን ከትናንት በስቲያ ማስተላለፉን በዘገባችን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ድረ ገፃችን በጉዳዩ ዙርያ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኡቴሳ ኡጋሞን አናግራ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተውናል።

” እኔ ወደ ክለቡ አዲስ ተሿሚ ሆኜ ከመጣሁ በኃላ ጉዳዩን ለመፍታት በሒደት ላይ ነበርን። ክለቡ የተጫዋቹን ጉዳይ ተመልክቶ ለመክፈል ወስነን ነበር፡፡ እኛም ሆንን ተጫዋቹ ከወላጅ አባቱ ጋር መጥቶ በተስማማነው ልክ ልንከፍለው ወደ ቦርድ ጉዳዩ ተላልፎም ነበር፡፡ ነገር ግን ቦርዱ ፈጥኖ ባለመቀመጡ እና ተጫዋቹም በመቸኮሉ የተፈጠረ ችግር ነው። በድርድር ላይ ነበርን፤ ተስማምተን እያለ የተፈጠረ ነው። አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ለመፍታት ከተጫዋቹ ጋር ዛሬ ተነጋግረናል።

“የሀዋሳ ቦርድ ትናንት በአፋጣኝ ተሰብስቦ የወሰነ ሲሆን የፊታችን ሰኞ የተጫዋቹ የአስራ አንድ ወር ደመወዝ ተፈፃሚም ይሆናል። ተጫዋቹ ወጣት እና ገና ታዳጊ በመሆኑ የቀደሙት የክለቡ ሥራ አስኪያጅ እና አሰልጣኝ የሰሩትን ስህተት ረስተን በድጋሚ ችግሮች ተፈተው ክለቡን ማገልገል እንዲችልም ፍላጎታችን ነው፡፡”


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!