ሲዳማ ቡና የእግድ ውሳኔ ተላለፈበት

በተጫዋቹ ሙጃሂድ መሐመድ ክስ ቀርቦበት የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ አላደረገም በሚል ሲዳማ ቡና ከፌዴሬሽኑ ማንኛውም አገልግሎት እንዳያገኝ ታግዷል።

በ2011 አጋማሽ ላይ ሙጃሂድ መሐመድ በሲዳማ ቡና ማልያ እየታጫወተ ሳለ ጉዳት ያጋጥመዋል። ለስድስት ወር ከሜዳ እርቆ ከጉዳቱ አገግሞ ሲመለስ ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት ቢኖረውም ክለቡ በ2012 የውድድር ዘመን ከቡድኑ ይቀንሰዋል። ተጫዋቹም ይህ የተቀነስኩበት መንገድ ተገቢ አይደለም የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት አለኝ በማለት ለፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ያሰማል። የተጫዋቹ ጉዳይ የተመለከተው የዲሲፒሊን ኮሚቴ ለተጫዋቹ ወደ ክለቡ እንዲመለስ ውሳኔ ያሳልፋል።

ሲዳማ ቡና ክለብ በአንፃሩ ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤ ያስገባል። በመጨረሻም ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም የሲዳማን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ሙጃሂዲድን ወደ ክለባቸው እንዲመልሱ እና ያልተከፈለው ደሞዙ እንዲከፈለው የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል።

ሆኖም እስካሁን በተሰጠው ጊዜ ተግባራዊ እንዲያደርግ የተላለፈውን ውሳኔ ሲዳማ ቡና ተፈፃሚ አላደረገም በሚል ከፌዴሬሽኑ ሲዳማ ቡናን ፌዴሬሽኑ ከሚሰጣቸው ማንኛውንም አገልግሎት እንዳያገኝ አግዶታል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!