አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

ከአዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች ጋር በመስማማት ላይ የተጠመዱት አዳማ ከተማዎች ሁለት የቀኝ መስመር ተጫዋቾችን በአንድ ዓመት ውል ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡

አንደኛው ፈራሚ ታፈሰ ሰርካ ነው፡፡ ይህ የቀደሞ የደቡብ ፖሊስ የመስመር ተከላካይ የልጅነት ክለቡን ለቆ ወደ መከላከያ ካመራ በኃላ እስከ 2011 በክለቡ አሳልፏል፡፡ የቀድሞው አሰልጣኙ ገብረመድኅን ኃይሌን ተከትሎ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በመጓዝም ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ወደ አዳማ ለማምራት ተስማምቷል፡፡

ሁለተኛው ፈራሚ አክሊሉ ተፈራ ነው፡፡ ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ በከፍተኛ ሊግ ወልቂጤ ከተማ ሲወዳደር በነበረበት ወቅት በክለቡ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ልጅነት ክለቡ ሀዋሳ ከተማ 2011 ክረምት ላይ ከተቀላቀለ በኃላ ለሁለት ዓመታት በሀይቆቹ መለያ ተጫውቷል፡፡ውሉ ከሀዋሳ ጋር መጠናቀቁን ተከትሎም ለአዳማ ለመጫወት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ባገኘችው መረጃ መሠረት በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊግ ከሰሞኑ ለማስፈረም እየተስማማ ሲሆን በቅርቡ የሙከራ ተጨማሪ ጊዜ ለተጫዋቾቹ የሚሰጥ በመሆኑ ለሚዲያ ይፋ ከማድረግ እንደተቆጠበ ሰምተናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!