ከኮቪድ 19 በኃላ ውድድሮች ሲጀመሩ አሰልጣኞች በሚያደርጓቸው የስልጠና መንገዶች ዙሪያ የኤዥያ እና የፊፋ ኢንስትራክተር እንዲሁም የጆርዳን ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት መሐመድ ጣሂር ትምህርታዊ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት በተጋበዥ እንግዳ አማካኝነት የሀገራችን አሰልጣኞች ከኮቪድ 19 በኃላ ውድድሮች ሲጀመሩ ማድረግ ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ነው፡፡ ከሦስት ሰዓታት በላይ የተሰጠው ስልጠናን በተጋባዥነት የሰጡት የኤዥያ እና የፊፋ ኢንስትራክተር የሆኑት መሐመድ ጣሂር በተጨማሪም የጆርዳን ዩኒቨርሲቲ የፊትነስ መምህር እና ኤክስፐርት ሲሆን ለኤዥያ ሀገራት ያቀረቡትን ገለፃ ነው ለእኛም ሀገር ዛሬ አመሻሽ የሰጡት፡፡
አሰልጣኞች ከኮቪድ 19 በኃላ ተጫዋቾቻቸውን ለዝግጅት ሲያገኟቸው ምን ማድረግ አለባቸው፣ የአካል ብቃት ልምምዳቸው ምን መሆን አለበት፣ በምን መልኩስ በኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ መደረግ ይገባዋል በሚል በአካል ብቃት ላይ በልዩ መልኩ ትኩረት ባደረገው የዛሬው ስልጠና አሰልጣኞች ከዚህ ቀደም ከሚያደርጉት ቅድመ ዝግጅት የአሁኑ ከባድ ሊሆን ስለሚችል በሰፊው ሊዘጋጁበት እንደሚገባ በዝርዝር አስረድተዋል። የክለብ ተጫዋቾች ረጅም ጊዜ በወረርሺኙ ምክንያት ከሜዳ ርቀው መቆየታቸውን ተከትሎ ሊከተሉት ስለሚገባ ልዩ የሆነ የስልጠና መንገድ ተጋባዡ ባለሙያ አፅንኦት የሰጡበት ጉዳይ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ለመረዳት ችላለች፡፡
ይህን ወይይት የፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞችን ጨምሮ ከሠላሳ በላይ የእግር ኳሱ ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!