የደቡብ-ምስራቅ ዞን ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዙር በሀዋሳ ከተማ መሪነት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን 1ኛ ዙር ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ ድል ሲቀናቸው ሲዳማ ቡና ለመጀመርያ ጊዜ ተሸንፏል፡፡

አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከተማ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ የአዳማ ከተማን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈችው አስካለ ገብረጻድቅ ናት፡፡ ድሉ አዳማን ከመጨረሻ ደረጃው አላቆ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጠው የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ሽንፈት ያስተናገደው ሲዳማ ቡና መሪነቱን ለሀዋሳ ከተማ አስረክቧል፡፡

ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን 3-1 አሸንፎ የዞኑን መሪነት ጨብጧል፡፡ የሀዋሳን የድል ግቦች አይናለም አሳምነው (ሁለት) እና ትዕግስት ወርቁ ሲያስቆጥሩ ባንቺአየሁ ደምሴ የጥሩነሽ ዲባባ ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡ ውጤቱ ሀዋሳን በ11 ነጥብ የዞኑ መሪ ሲያሰርገው ጥሩነሽ ዲባባን ግርጌ ላይ አስቀምጦታል፡፡

በ10፡00 ድሬዳዋ ላ አርባምንጭ ከተማን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ ካለግብ ጨዋታውን አጠናቋል፡፡ ውጤቱ አርባምንጭን 3ኛ ድሬዳዋ ከተማን 4ኛ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡

የዞኑ ደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-

Untitled

 

ያጋሩ