ተስፋ ሊግ ፡ ቡና ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ጊዮርጊስ መሪውን ተጠግቷል

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ተስፋ ሊግ የ8ኛ ሳምንት 3 ጨዋታዎች ትላንት ተካሂደዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነቱ የተመለሰበትን ውጤት ሲያስመዘግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪው ንግድ ባንክን ተጠግቷል፡፡

3፡00 ላይ ሰውነት ቢሻውን የገጠመው ኢትዮያ ቡና 2-0 በማሸነፍ አንሰራርቷል፡፡ የቡናን የድል ግቦች አዲስ ፍስሃ እና ጳውሎስ መላኩ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ውጤቱ ቡናን ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ሲያሰደርገው ሰውነት ቢሻውን ካለምንም ነጥብ በ25 የግብ እዳ የመጨረሻውን ደረጃ እንዲይዝ አስገድዶታል፡፡

በ05፡00 ሙገር ሲሚንቶ ከአዳማ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ካለግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ በጨዋታው ሙገሮች የፍፁም ቅጣት ምት አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡

07፡00 ላይ መድንን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 በማሸነፍ ወደ 2ኛ ደረጃ አድጓል፡፡ የጊዮርጊስን ሁለቱንም የድል ግቦች ዮሃንስ ታደሰ ሲያስቆጥር ሙባረክ ታደሰ የመድንን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የ8ኛ ሳምንት አጠቃላይ ውጤቶች

ቅዳሜ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ

ደደቢት 1-1 መከላከያ

እሁድ

ኢትዮጵያ ቡና 2-0 ሰውነት ቢሻው

አዳማ ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 ኢትዮጵያ መድን

-ኤሌክትሪክ በዚህ ሳምንት ለ2ኛ ጊዜ አራፊ ቡድን የሆነ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ተስተካካይ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል፡-

tesfa

 

ያጋሩ