ፊፋ ወርሃዊ የብሔራዊ ቡድኖችን ደረጃ ይፋ አድርጓል

ከደቂቃዎች በፊት የሀገራት ወርሃዊ የእግርኳስ ደረጃ ሲወጣ ኢትዮጵያም የተቀመጠችበት ደረጃ ታውቋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት የሃገራት የእግርኳስ ውድድሮች ለ6 ወራት ከተቋረጡ በኋላ ዳግም መመለሳቸው ይታወቃል። የሃገራትን ወርሃዊ የእግርኳስ ደረጃ የሚያወጣው ፊፋ ደግሞ ዛሬ ረፋድም የአባል ሀገራቱን ደረጃ ይፋ አድርጓል። በዚህም ቤልጂየም፣ ፈረንሳይ እና ብራዚል በተቀመጡበት ከ1-3ኛ ደረጃ ላይ ሆነው የዓለም ቁንጮ መሆናቸውን አስቀጥለዋል።

ሴኔጋል በበኩሏ ከዓለም 20ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 1ኛ ሆና ተቀምጣለች። ሴኔጋልን ተከትለው ቱኒዚያ እና ናይጄሪያ ከዓለም 26ኛ እና 29ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ ሆነዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ 1061 ነጥቦችን በማገኘት ከ210 ሀገራት 146ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በአህጉራችን አፍሪካ ከሚገኙ 54 ሀገራት ደግሞ 13 ሀገራትን ብቻ በልጣ 41ኛ ደረጃን ይዛ ተቀምጣለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!