ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ከተማ የአሰልጣኙን ውል ለማራዘም ተስማማ

አሰልጣኝ አሥራት አባተ በቡታጅራ ከተማ ለመቆየት ዛሬ ተስማማ፡፡

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበሩ ክለቦች መካከል በምድብ ሐ የሚገኘው ቡታጅራ ከተማ ይጠቀሳል። ቡድኑ በአርባምንጭ ከተማ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች እስኪበለጥ ድረስ በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጡ የሚታወስ ሲሆን ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመራ ውጤታማ ጉዞ ያደረገው አሰልጣኝ አሥራት አባተ ከቀናት በፊት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ የበላይ አካላት ጋር በተደረገ ድርድር ዘንድሮም በድጋሚ በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም የደደቢት እና የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ቡድኖችን ከዚህም በተጨማሪ በወንዶች አዲስ አበባ ከተማ እና ቢሾፍቱ ከተማን ማሰልጠኑ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!