የፕሪምየር ሊጉ የብሮድካስት ክፍፍል እንዴት እንደሚሆን ተገለፀ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከቴሌቭዥን፣ ሬድዮ እና ከሊጉ ሥያሜ የሚገኘውን ገንዘብ እንዴት እንደሚያከፋፍል ገለፃ አደገ።

አክሲዮን ማኅበሩ በአሁኑ ሰዓት እየሰጠው ባለው መግለጫ ላይ በአንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ የተነሱ ጉዳዮችን ለጋዜጠኞች ገለፃ እያደረገ ይገኛል። ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ማኅበሩ ከሊጉን ስያሜ፣ ቴሌቭዥን እና ሬዲዮ መብት የሚገኘውን ገቢ ለክለቦች እንዴት እንደሚከፋፈል እና ጉባኤው ተወያይቶ ውሳኔዎች የተወሰኑባቸውን መለኪያዎች ይፋ አድርጓል።

ማኅበሩ በሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው ጨረታ መሰረት የተባሉት ነገሮች ገቢ የሚያመጡ ከሆነ በሚከተሉት መለኪያዎች ክፍፍሎች ይፈፀማሉ።

1- አስራ ስድስቱም የሊጉ ክለቦች ከሚገኘው ገቢ 50% የሚሆነውን ይከፋፈላሉ። ምክንያቱም የአክሲዮን ማኅበሩ አባል ስለሆኑ።

2- ከሚገኘው ገቢ 15% የሚሆነው ለሊግ ካምፓኒው እንዲተው ይደረግና ቀሪው ድርሻ ክለቦቹ ባገኙት ደረጃ መሰረት እንዲሰጣቸው ይደረጋል።

3- የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ መብቱን የሚገዛው ተቋም በሚመርጣቸው እና አንድ ክለብ በዓመቱ የተላለፉለትን ጨዋታዎች ታሳቢ ተደርጎ ይሰጣል።

ከሥያሜው መብት የሚገኘውን ገቢ ለውድድር አሸናፊዎች እና ኮከቦች የሚሰጠውን ሽልማት እንዲሸፍን ይደረጋል። በዚህም የሉጉ አሸናፊ ክለብን ጨምሮ የሊጉ ኮከቦች ከዚህ ቀደም ከሚያገኙት የሽልማት ገንዘብ የተሻለ እንዲያገኙ ይደረጋል።

የአክሲዮን ማኅበሩ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ”የስያሜ መብቱን ለመግዛት የሚመጣው ተቋም የክለቦችን ስፖንሰር የሚጨቁን (የሚመሳሰል) ከሆነ ስፖንሰር ሺፑን አንቀበልም” ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ሊጉ ከተቋረጠ በኋላ የማኅበሩ የቦርድ አመራቶች ትላልቅ የሃገራችን ተቋማት ጋር ሄደው የሊጉን ስያሜ እንዲገዙ እንደጠየቁ ነገርግን እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!