ወልቂጤ ከተማ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አድርጓል

ወልቂጤ ከተማዎች በቀጣዩ ሳምንት የ2013 ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ፡፡

በተሰረዘው ውድድር ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ አድገው መልካም እንቅስቃሴ ያሳዩት ወልቂጤዎች የዋና አሰልጣኝ ውል አራዝመው አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ የሚገኙ ሲሆን የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአሰልጣኝ ደግአረግ እየተመሩ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራሉ፡፡ ጥቅምት 10 እና 11 የክለቡ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች እና የቡድኑ አጠቃላይ አባላት ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን ሀሙስ እና አርብ የኮቪድ 19 ምርመራን የሚደርጉ ይሆናል። የምርምራው ውጤት መሠረት በማድረግም በቀጣይ ሳምንት የቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደሚጀምሩ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!