የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በትናትናው ዕለት የቴክኒክ ኮሚቴው በቃለ ጉባኤ ተፈራርሞ ያቀረበውን ባለ ዘጠኝ ነጥብ ሰነድ ከመረመረ በኃላ አሰልጣኙ ማን እንደሆነ አንግለፅ እንጂ አሰልጣኙን መርጦ ለመቅጠር መወሰኑን ማሳወቃችን ይታወቃል። በትናትናው ዕለት በነበረው ስብሰባ የተለያዩ አስገራሚ ክስተቶች ተፈጥረዋል።
* የቴክኒክ ኮሚቴው ምክረ ሀሳብ ምንም አይነት የአማራጭ ሀሳብ የሌለው እና ለአንድ ግለሰብ የወገነ ነው በማለት ምክረ ሀሳቡን ውድቅ ስለመደረጉ ተሰምቷል።
* ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል።
* በሥራ አስፈፃሚዎቹ በኩል የቃላት ምልልሶች እና ሽኩቻዎች ተስተናግደውበት አልፈዋል።
* አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንዲሆኑ በድምፅ ብልጫ ተወስኗል።
* ምን አልባት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ካልቻሉ አማራጭ ተጠባባቂ አሰልጣኞች ተይዘዋል።
* ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን ከኃላፊነት ሊያነሱ የሚችሉበት መንገድ እንዳለ ተሰምቷል።
በአጠቃላይ በቀጣይ የሚፈጠሩ ነገሮች ምድናቸው የሚሉትን ጉዳዮች ተከታትለን እናቀርባለን።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!