Soccer Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአርባ ተጫዋቾች ጥሪ አደረገ

Share

አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ40 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡፡

የዋልያዎቹ አለቃ አሰልጣኝ ውበቱ ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከቡ ከቀናት በኃላ በቀጣይ ወር ከኒጀር ጋር ለሚኖራቸው የደርሶ መልስ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ይረዳቸው ዘንድ ምክትሎቻቸው ደሳለኝ ገ/ጊዮርጊስን በግብጠባቂ አሰልጣኝ እንዲሁም አንዋር ያሲን እና አሥራት አባተን በም/አሰልጣኝ ከመረጡ በኃላ ለአርባ ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

* ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል በአሁን ሰዓት በግብጽ ሊግ ከሚጫወተው ሽመልስ በቀለ በስተቀር 39ኙም ተጫዋቾች በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ናቸው፡፡

* ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መስከረም 23 ቀን ከጠዋቱ 03:00 እስከ 04:00 ድረስ ሪፖርት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል።

* በዕለቱም መስከረም 23 ቀን ወድያውኑ የኮቪድ ምርመራ እንደሚደረግላቸው ታውቋል፡፡

*ዝግጅታቸውን በካፍ አካዳሚ የሚያደርጉ ሲሆን፤ ፌዴሬሽኑም ካፍ አካዳሚን ዝግጁ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል።

* ጥሪ ከተደረገላቸው መካከል ሰዒድ ሀብታሙ (ግብጠባቂ) እናኃይለሚካኤል አደፍርስ (ተከላካይ) ለመጀመርያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ ናቸው።

* ዳዊት እስጢፋኖስ ከረጅም ዓመት በኃላ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ዳግመኛ የመጠራት እድል ሲያገኝ ጌታነህ ከበደ እና መስዑድ መሐመድ ከረጅም ጊዜ በኃላ ባይሆንም ከቅርብ ርቀት በኃላ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ሆነዋል።

* ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ ጋዲሳ መብራቴ፣ ሱሌይማን ሰሚድ እና በረከት ደስታ ስማቸው በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ዝርዝር ውስጥ ብዙም የማይካተቱ አሁን ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋች ሆነዋል።

* ፋሲል ከነማ ዘጠኝ ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰምንት፣ ኢትዮጵያ ቡና በሰባት ቀጣዮን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

* በተለይ ሙጂብ ቃሲም፣ ኤፍሬም ዓለሙ እና ወንድሜነህ ደረጄ በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ጥሪ ሳይቀርብላቸው በመቅረቱ ብዙዎችን ቢያነጋግርም አሁን ዳግመኛ የመጠራቱን እድል አግኝተዋል።

* ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር እየተጫወቱ ጥሪ ይደረግላቸው የነበሩ ጋቶች ፓኖም፣ ኡመድ ኡኩሪ እና ቢንያም በላይ ጥሪ ያልተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ግብጠባቂዎች

አቤል ማሞ፣ ግብ፣ ምንተስኖት አሎ፣
ይድነቃቸው ኪዳኔ ፣ ተክለማሪያም ሻንቆ እና ሰኢድ ሀብታሙ

ተከላካዮች

ረመዳን የሱፍ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ኃይለሚካኤል አደፍርስ፣ አህመድ ረሺድ፣ ሱሌማን ሰኢድ፣ አስቻለው ታመነ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ያሬድ ባየህ፣ ወንድሜነህ ደረጀ፣ መሳይ ጳውሎስ እና ደስታ ደሙ

አማካይ

ሽመልስ በቀለ፣ ይሁን እንደሻው፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ፍፁም ዓለሙ፣ አማኑኤል ዮሀንስ፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ መስዑድ መሐመድ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ሀይደር ሸረፋ

አጥቂዎች

አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ ጋዲሳመብራቴ ፣ አዲስ ግደይ፣ በረከት ደስታ፣ ሽመክት ጉግሳ፣ ሃብታሙ ገዛኸኝ፣ አቤል ያለው፣ ሚኪያስ መኮንን፣ አቡበከር ናስር፣ ሙጂብ ቃሲም፣ መስፍን ታፈሰ፣ ባዬ ገዛኸኝ እና ጌታነህ ከበደ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top