ከፍተኛ ሊግ | አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኙን ለማቆየት ተስማማ

መሳይ ተፈሪ ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በአርባምንጭ ለመቆየት ተስማማ፡፡

በተሰረዘው የ2012 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ላይ ከሚወዳደሩ ጠንካራ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሉጉ ለመመለስ በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እየተመራ ባስመዘገባቸው ውጤቶች እስከ 11ኛው ሳምንት የሊጉ መቋረጥ ድረስ በአንደኝነት ሲመራ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁን እና ክለቡ ለዘንድሮው የ2013 የውድድር ዓመት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ክለቡን እንደሚለቁ ለድረ-ገፃችን የገለፁ ቢሆንም አሁን ግን ከክለቡ ጋር በተደረገ ድርድር ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት መድረሳቸውን አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እና የክለቡ ስራ-አስኪያጅ አቶ ስንታየው ንጉሴ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ 

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከዚህ በፊት በወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ አሰልጥነው ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

እንደ ስራ አስኪያጁ አቶ ስንታየው ገለፃ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ሆነ ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ውል ከዛሬ ጀምሮ በማስፈረም እና ወደ ማደሱ ተግባር እንደሚገቡ ጨምረው ነግረውናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!