የሎዛ አበራ የማልታ ቆይታ ?

ቢርኪርካራዎች ያለ ሎዛ አበራ ውድድራቸውን ጀምረዋል።

በቅርቡ የተሞሸረችው ሎዛ አበራ ባለፈው የውድድር ዓመት ድንቅ ጊዜ ወዳሳለፈችበት ቢርኪርካራ እስካሁን ያልተመለሰች ሲሆን ክለቡም አጥቂዋን ሳይዝ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ ሁለት ለባዶ አሸንፏል። ሎዛ ከክለቡ ጋር ያላትን ውል የማራዘምም ሆነ የመለያየትዋ ጉዳይ ቁርጡ ያልለየለት ጉዳይ ቢሆንም የጎል አነፍናፊዋ ውሏን የምታራዝምበት ዕድል ጠባብ እንደሆነ መስማት ችለናል። ተጫዋቿ በዚህ ሰዓት በአውሮፓ የተሻሉ አማራጮችን በማየት ላይ ስትሆን ከዛ በተጨማሪም ከአንዳንድ የሃገር ውስጥ ክለቦች ጋር ስሟ እየተያያዘ ይገኛል።

ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት አዳማ ከተማን ለቃ ወደ ማልታ በማቅናት ሊጉ በኮቪድ ምክንያት እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 30 ጎሎችን አስቆጥራ የማልታ ሊግን ከክለቧ ጋር እንዲሁም በግሏ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ክብርን ማሸነፏ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!