ሽመክት ጉግሳ በፋሲል ከነማ ውሉን አራዘመ

በክረምቱ በዝውውር ጉዳይ አነጋጋሪ ከሆኑ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሽመክት ጉግሳ በመጨረሻም በፋሲል ከነማ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

የቀድሞው የወላይታ ድቻ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ደደቢት የመስመር አጥቂ ወደ ዐፄዎቹ ካመራ በኋላ ሁለት የተሳኩ የውድድር ዓመታት ያሳለፈ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቡ ለመቀጠል ተስማምቶ ኋላ ላይ ደግሞ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት መስማማቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ የዝውውር መስኮቱ በይፋ መከፈቱን ተከትሎ በፋሲል ከነማ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል በፌዴሬሽን ተገኝቶ ፈርሟል።

“ፋሲሎች ለእኔ የነበራቸው ነገር ትልቅ ስለነበር እኣ አመራሮቹንም ሆነ ደጋፊውን ማጣት ስለከበደኝ ለማራዘም ወስኛለሁ። በወላይታ ድቻ በተስማማሁት መሰረት የጠበኩትን ነገር ባላገኝም ከፋሲል ጋር የነበሩትን ችግሮች ተነጋግረን በመፍታታችን ወደምወደው ክለቤ ደስ ብሎኝ ተመልሻለሁ” ሲል ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!