ወልቂጤ ከተማ አጥቂ አስፈረመ

ወልቂጤ ከተማ የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ሄኖክ አየለን አስፈርሟል።

በደቡብ ፖሊስ የእግርኳስ ሕይወቱን ጀምሮ በአዳማ ከተማ፣ ዲላ ከተማ እና አሁን በድጋሚ ለተቀላቀለው ወልቂጤ ከተማ የተጫወተው ሄኖክ በ2011 ከደቡብ ፖሊስ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉን ተከትሎ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ወደ ሀዋሳ ከተማ በማቅናት ሲጫወት ቆይቷል። በክለቡም ለመቆየት ቅድመ ስምምነት አድርጎ የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን ቡድን በአንድ ዓመት ኮንትራት ተቀላቅሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!