ከፍተኛ ሊግ | ነቀምቴ ከተማ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም ፕሬዝዳንቱ ከኃላፊነታቸው ለቀዋል

በተቋረጠው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ነቀምቴ ከተማ የአሰልጣኙን ውል ሲያድስ የክለቡ ፕሬዝዳንት በምክትላቸው ተተክተዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ክለቡን በአሰልጣኝነት እየመሩ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ላይ የሚገኙት አሰልጣኝ ቾምቤ ገ/ህይወት ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ለተጨማሪ ለአንድ ዓመት ውላቸውን አድሰዋል። አሰልጣኝ ቾምቤ ባለፈው ዓመት የምድቡ መሪ የነበረውን ክለብ ጥንካሬ በማስቀጠል ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊግ የማሳደግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

ያለፉትን ሦስት ዓመታት ክለቡን በፕሬዝዳንት በመምራት ክለቡ እንዲሻሻል የረዱት አቶ ደረጄ ሙላት ኃላፊነታቸውን ለቀዋል። ክለቡ በተለይ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአነስተኛ በጀት ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን፣ የተረጋጋ የፋይናንስ ስርአት ካላቸው የሀገሪቷ ክለቦች ተርታ እንዲጠቀስ ወሳኙን ሚኔ ተጫውተዋል፡፡ በአቶ ደረጄ ምትክ በጊዜያዊነት ምክትላቸው አቶ ቸርነት አራጎ በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!