ሰበታ ከተማ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አወጣ

ሰበታ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር በዛሬው ዕለት የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሳልፎ የሰጠው ሰበታ ከተማ አዲስ ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያን ከዛሬ መስከረም 29 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 3 በሚቆይ የቀን ገደብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ማስታወቂያ ማውጣቱን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ምንዳ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሥራ አስኪያጁ የካፍ ኤ ላይሰንስ እና የፕሪምየር ሊግ ልምድ ያለው በይበልጥ ተፈላጊ በመሆኑ መወዳደር እንደሚችልም ነግረውናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!