የጣና ሞገዶቹ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

የዝውውር መስኮቱ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ለሁለት ክለቦች ለመፈረም ተስማምቶ የነበረው ባዬ ገዛኸኝ በመጨረሻም መዳረሻውን ባህር ዳር ከተማ አድርጓል።

ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ከተያያዘ በኋላ በወላይታ ድቻ ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ የነበረው ይህ የአጥቂ መስመር ተጫዋች ከሳምንታት በፊት ለወልቂጤ ከተማ ፊርማውን ቢያኖርም ውሉ በፌዴሬሽን ዘንድ ቀርቦ አለመፅደቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት በይፋ ለባህር ዳር ከተማ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ይህ የቀድሞ የስልጤ ወራቤ፣ መከላከያ ፣ ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ተጫዋች ዓምና ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 9 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር። ተጫዋቹም የአጥቂ መስመራቸው ላይ መሳሳት እያሳዩ ለሚገኙት የጣና ሞገዶቹ ጥሩ አማራጭ ለመሆን ስብስቡን ተቀላቅሏል።

ባህር ዳር ከተማዎች ከዚህ ቀደም መናፍ ዐወል፣ አህመድ ረሺድ፣ በረከት ጥጋቡ እና አፈወርቅ ኃይሉ ለሁለት ዓመታት የግላቸው ለማድረግ ተስማምተው እንደነበረ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ