ካፍ የኢንስትራክተሮችን ደረጃ አጸደቀ 

 

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን/ካፍ/ እ.አ.አ ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም የአሰልጣኝ ኢንስትራክተርነት ደረጃ ያጸደቀላቸውን የኢትዮጵያ አሰልጣኞች ዝርዝር ሰሞኑን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ልኳል፡፡

በሚስተር አብደል ሞኒየም ሁሴይን ሻታ የካፍ እግር ኳስ ልማት ዳይሬክተር በተላከው የኢትዮጵያ አሰልጣኝ ኢንስትራክተሮች ዝርዝር መሰረት አብርሃም መብራቱ፣ አብርሃም ተክለሃይማኖት፣ አንተነህ እሸቴ፣ መኮንን ኩሩ፣ ዶ/ር ጌታቸው አበበ፣ሰውነት ቢሻው በአዲሱ የካፍ ኢንስትራከተሮች አጽዳቂ አካል የኢንስትራክተርነት ማእረግ ጸድቆላቸዋል፡፡

ሌሎች በፌደሬሽኑ ስር የሚገኙ ኢንስትራክተሮች በፌደሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሃላፊነት አማካኝነት የትምህርትና የስልጠና ዝግጅታቸው እየተገመገመ በሀገር ውስጥ እውቅና እንደሚሰጣቸው ከካፍ የተላከው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

(ዜናው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው)

ያጋሩ