ሲዳማ ቡና ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

ሲዳማ ቡና የ2013 የውድድር ዓመት ዝግጅቱን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር አመት ታህሳስ 3 እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዛሬ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ የገለፀ ሲሆን ክለቦችም ወደ ልምምድ መግባት እንዲችሉ ይፋ አድርጓል፡፡በዚህም መሠረት ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅድመ ዝግጅት ለመጀመር ሲዳማ ቡና ቀኑን ይፋ ማድረጉን የክለቡ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ጥቅምት 2 እና 3 የክለቡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና ጠቅላላ የቡድኑ አባላት የሜዲካል ምርመራ እንዲሁም የኮቪድ 19 ምርመራን በማድረግ ሁለቱንም የጤና ምርመራዎች አልፈው ነፃ የሚሆኑ አባላት በጠቅላላ ወደ ካምፕ ከገቡ በኃላ ጥቅምት 5 በሀዋሳ ስታዲየም ልምምዳቸውን ለመጀመር መዘጋጀታቸውን አሰልጣኙ ነግረውናል፡፡

ሲዳማ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ቀጥሎ ሦስተኛው የዝግጅት ጊዜውን ያሳወቀ ክለብ ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!