በ2010 ለደደቢት ሲጫወት በነበረው ብርሀኑ ቦጋለ ክስ የቀረበባቸው ደደቢቶች በፌዴሬሽኑ የታገዱ ሲሆን በቀድሞው የሴት ቡድኑ ተጫዋቾችም ቅሬታ ቀርቦባቸዋል፡፡
በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በርከት ያሉ ክለቦች ከተጫዋቾች ደመወዝ ካለ መክፈል ጋር በተገናኘ የተለያየ የእግድ ውሳኔ እየተላለፈባቸው የሚገኝ ሲሆን የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ደደቢት ሌላኛው ውሳኔውን ተፈፃሚ እስኪያደርግ የታገደ ክለብ መሆኑን የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ገልፀውልናል፡፡ ክለቡ ይህ ውሳኔ የተላለፈበት በ2010 ለክለቡ ሲጫወት የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ብርሀኑ ቦጋለ ከአምስት ወራት በላይ ደመወዝ አልተከፈለኝም በሚል ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ መሆኑን ኃላፊው ነግረውናል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ በክለቡ ከ2010 እስከ 2011 ውል የነበራቸው ሴት ተጫዋቾች ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ የደደቢት ሴቶች ቡድን ከ2010 የውድድር ዓመት ፍፃሜ በኋላ ቢበተንም በወቅቱ ይጫወቱ የነበሩ ተጫዋቾች ደመወዝ እና የሽልማት ገንዘብ እንዳልተሰጣቸው በመግለፅ የክስ ወረቀትን ለፌዴሬሽኑ ስለማስገባታቸው አውስተው ምላሽ በመጠበቅ ላይ እንደሆኑ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!