የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ወደ አፋር ተጉዘው ድጋፍ አድርገዋል

በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በተመታው የአፋር ክልል የተለያዩ ቀበሌዎች ለሚገኙ ወገኖች የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ወደ ክልሉ ተጉዘው ድጋፍ አድርገው ተመልሰዋል።

ከሳምንት በፊት በአፋር ከተማ የአዋሽ ወንዝ መሙላቱ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች ቤታቸው ወድሞባቸው፣ ለፀሐይ፣ ለብርድ፣ ለረሀብ እና ለውሃ ጥም የተዳረጉት ወገኖቻችንን ለመርዳት በራሳቸው ተነሳሽነት በተለያዩ ደጋፊዎች አስተባባሪነት ላለፉት ቀናት ያሰባሰቡትን ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት የምግብ እህሎች፣ የአልባሳት ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመያዝ ከአዲስ አበባ 300 ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ድጋፍ አድርገዋል።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለአፋር ጎርፍ ተፈናቃዮች የአምስት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!