ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተለያየው የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አዲስ ክለብ አግኝቷል

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ እና አሰልጣኝ ኒዲይዚ ኤሚ የሩዋንዳውን ክለብ በሁለት ዘርፎች ለማገልገል አምርቷል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውስጥ በግብ ጠባቂነት በክለቡ ከተጫወቱ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል የብሩንዲ ዜግነት ያለው ኒዲይዚ ኤሚ ተጠቃሹ ነው፡፡ ግብ ጠባቂው በፈረሰኞቹ መለያ ክለቡን በግብ ጠባቂነት አገልግሎ ካለፈ በኃላ ከ2003 ጀምሮ የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በመሆን እስከተሰረዘው የውድድር ዓመት ድረስ ያገለገለ ሲሆን ክለቡ ለውጥ ለማድረግ በማሰብ በጠቅላላው የአሰልጣኝ ቡድን አባላቶቹን ሲለውጥ ይህም አሰልጣኝ የዚህ ዕጣ ፈንታ ቀማሽ በመሆኑ ከክለቡ መለያየቱ ይታወሳል፡፡

ይህ ብሩንዳዊ ወደ ሩዋንዳ አምርቶ ኪዩቡ ስፖርትስ በተባለው ክለብ በቴክኒክ አስተባባሪነት እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ተሹሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!