ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

በሳምንቱ መጀመሪያ የዝውውር ገበያውን በይፋ የተቀላቀለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደቂቃዎች በፊት ተጨማሪ ወሳኝ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።

ሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታህሳስ 10 በሚጀመረው የ2013 የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ራሱን እያጠናከረ ይገኛል። ሰኞ ዕለትም ሰናይት ቦጋለ እና አያንቱ ቶሎሳን አስፈርሞ ገበያውን ተቀላቅሎ ነበር። ዛሬ ደግሞ በቅርብ ዓመታት ድንቅ ብቃቷን እያሳየች የምትገኘውን አረጋሽ ካልሳን በይፋ ማስፈረሙ ተረጋግጧል።

2008 ላይ ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ በመግባት ራሷን ለአራት ዓመታት ካበቃች በኋላ ወደ መከላከያ ተጉዛ ጠንካራነቷን ያሳየችው አረጋሽ በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራውን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለማገልገል ፊርማዋን በፌዴሬሽን ተገኝታ አኑራለች። ተጫዋቿ በክለብ ደረጃ ከምታሳየው ጥሩ ብቃት በተጨማሪ ሃገሯን በእድሜ እና ዋናው ቡድን ወክላ ማገልገሏ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!