ዜና እረፍት| የቀድሞ የዎላይታ ድቻ አምበል ህይወቱ አለፈ

ከዚህ ቀደም ዎላይታ ድቻን በአምበልነት የመራውና የወቅቱ የሶዶ ከተማ አምበል ፈጠነ ተስፋማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የተጫዋቹ ህልፈተ ሕይወት የተሰማው ዛሬ ወደ 5 ሰዓት ገደማ ሲሆን በድንገት በመኖሪያ ቤቱ አርፎ ተገኝቷል።

የእግርኳስ ህይወቱን በሶዶ የፕሮጀክቶች ሥልጠና ውስጥ የጀመረው ፈጠነ ተስፈማርያም በ2002 ዎላይታ ድቻ ሲቋቋም በአምበልነት የመራ ሲሆን ድቻ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክቷል። በመቀጠልም በሀድያ ሆሳዓና፣ ዲላ ከተማ እና ኮንሶ ኒውዮርክ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ህልፈተ ህይወቱ እስኪሰማ ድረስ በከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ሶዶ ከተማ በአምበልነት እያገለገለ ነበር። ፈጠነ ተስፈማርያም በእግርኳስ ህይወቱ በተለያየ ጊዜ የዎላይታን ዞን በመወከል በርካታ ግዜ ተሳትፏል።

ሶከር ኢትዮጵያም በተጫዋቹ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቡድን አጋሮቹ መጽናናትን ትመኛለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!