የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የኮሮና ምርመራ ውጤት…

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አምስት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ገልጾ ሚዲያዎች በቫይረሱ የተያዙትን ተጫዋቾች ማንነት ባለመግለፅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ያደረገው መረጃ ይህንን ይመስላል:-

– ትናንት ማምሻውን የኮቪድ 19 ምርመራ ካደረጉ 36 የቡድኑ አባላት መካከል 5ቱ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን፤ 5ቱም ራሳቸውን አግልለው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

– የተቀሩት 31 የቡድኑ አባላት ማምሻውን የካፍ አካዳሚ ገብተዋል። በነገው እለትም የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ከረፋዱ 3ሰዓት የሚጀምሩ ይሆናል።

– ከ72 ሰዓታት በኋላ ኮቪድ Negative የሆኑት ተጫዋቾች እና የቡድኑ አባላት በሙሉ ምርመራ የሚደረግላቸው ይሆናል።

– ቡድኑን ዘግይተው የተቀላቀሉት ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ እና ሱራፌል ዳኛቸው እንዲሁም የቡድኑ ወጌሻ በነገው እለት የኮቪድ ምርመራ የሚደረግላቸው ይሆናል።

ማሳሰቢያ

በተለያዩ አማራጮች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ተጫዋቾችን ዝርዝር የማግኘት እድሉ ያላችሁ የሚዲያ አካላትም ሆነ ግለሰቦች ለእያንዳንዱ ተጫዋች የግል ህይወት ነጻነት ሲባል እና በስነ ልቦናም እንዳይጎዱ የተጫዋቾቹን ስም ይፋ ባለ ማድረግ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!