ወልዋሎ አዲስ ሥራ አስከያጅ ቀጠረ

አቶ ሚካኤል ዓምደመስቀል አዲሱ የወልዋሎ ሥራ አስከያጅ ሆነው በይፋ ቦታውን ተረክበዋል።

ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ሹመቶች በደደቢት ሲሰሩ የቆዩት አዱሱ ሥራ አስከያጅ ከሳምንታት በፊት ወደ ወልዋሎ በማምራት እንቅስቃሴዎች ጀምረው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በይፋ ቦታውን ተረክበዋል። ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ የነበራቸው አቶ ሚካኤል ወልዋሎን የተሻለ ተፎካካሪ ለማድረግ የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀው በክለቡ እየታየ ያለው ተስፋ ያለው የታዳጊ ተጫዋቾች እድገት ማስቀጠልም ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑ ገልፀዋል። ሥራ አስከያጁ አክለውም ክለቡ የተጋነኑ ወጪዎች የማውጣት እቅድ እንደሌለው ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ወደ ዝውውሩ ያልገቡት ወልዋሎዎች ከነገ ጀምሮ እንቅስቃሴ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል። ላለፉት ቀናት በዓዲግራት የቆዩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደግዮርጊስም በዝውውር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከክለቡ ጋር ተወያይተዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!