የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታወቀ

ፕሪምየር ሊግ አ/ማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበትን ቀን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮቪድ 19 ቅድመ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከሁለት ወራት በኃላ እንዲጀመር የሊግ ካምፓኒው ዛሬ ከሰዓት ለክለቦች በላከው ደብዳቤ መግለፁን የሊግ ኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአስራ ስድስት ክለቦች መካከል በተመረጡ ስድስት ስታዲየሞች የሚደረገው ይህ የፕሪምየር ሊግ ውድድር በታህሳስ 3 እንደሚጀመር ኩባንያው አሳውቋል፡፡ በዚህም መነሻነት ክለቦች ይህን ቀን ታሳቢ በማድረግ ለተጫዋቾቻቸው እና ለቡድኑ አጠቃላይ አባላት ምርመራን ካደረጉ በኃላ ወደ ልምምድ መግባት እንደሚችሉም ኃላፊው ገልፀውልናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!