የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥተዋል

የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊዎቹ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዲያ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከወረደ በኃላ ያለፉት ሁለት አመታት በከፍተኛ ሊጉ እየተወዳደረ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌትሪክ ከአሰልጣኝ አንዋር ያሲን ጋር በመለያየት በጊዜያዊ አሰልጣኝ ሲመራ ከቆየ በኃላ ለዘንድሮው የ2013 የውድድር ዓመት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያን በዛሬው ዕለት አውጥቷል፡፡ ክለቡ በማስታወቂያው ምንም ፆታን ያለየ በመሆኑ ወንድም ይሁን ሴት አሰልጣኝ መስፈርቱን አሟላለው የሚል ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት መወዳደር እንደሚችል ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


በተመሳሳይ በፕሪምየር ሊጉ ከዚህ ቀደም ተወዳዳሪ የነበረውና በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ላይ የሚገኘው ወልዲያ ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ክለቡ ከመስከረም 26 ጀምሮ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ማስታወቂያውን ያወጣ ሲሆን እስከ ጥቅምት 3 ድረስ አሁንም አሰልጣኞች መወዳደር ይችላሉ ተብሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!