ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ አሰልጣኝ ሲለውጥ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

መከላከያ ለሴት ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ሲመድብ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ፡፡

መከላከያ ከሰሞኑ የቀድሞው የወንድ ቡድኑ አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳንን በዋና አሰልጣኝነት ቦታ መድቦ የነበረ ቢሆንም በቀናት ልዩነት በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ በአባልነት የሴት እና የታዳጊ ቡድኑን በማሰልጠን የሚታወቀው ስለሺ ገመቹ አዲሱ አሰልጣኝ ሆኖ ተመድቧል፡፡

ክለቡ ከዚህም በተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከአዳማ ከተማ ጋር ለመቀጠል ከሰሞኑ ቅድመ ስምምነት ልይ ደርሳ የነበረችው መስከረም ካንኮ ወደ ጦሩ አምርታለች። የቀድሞ የደደቢት ተከላካይ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአዳማ ቆይታ አድርጋ ነበር።

ሌላዋ የመከላከያ አዲስ ፈራሚ በተመሳሳይ ያለፉትን ዓመታት በአዳማ ያሳለፈችው የመሀል አማካይዋ ገነት ኃይሉ (ጄምባ) ስትሆን እንደመስከረም ሁሉ በሁለት ዓመት ውል ጦሩን ተቀላቅላለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ያጋሩ