ስሑል ሽረ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የተለያየው አሌክስ ተሰማ የስሑል ሽረ ፈራሚ ሆኗል፡፡

አንጋፋ የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ያለፉትን አራት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከክለቡ መለያየቱን እና በአንድ ክለብ ማረፊያውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ለሶከር ኢትዮጵያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም ከጥቂት ሰዓታት በፊት ለስሑል ሽረ ለመጫወት የአንድ ዓመት ውል ተፈራርሟል፡፡

ከዚህ ቀደም በኒያላ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ዳሽን ቢራ እና መቐለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ የአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም የክረምቱ የመጀመርያ ፈራሚ ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!