ኢትዮጵያ ቡና የመሐል ተከላካይ አስፈረመ

የመሐል ተከላካዩ አበበ ጥላሁን ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቀለ፡፡

የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተከላካይ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ሲዳማን በመልቀቅ በመከላከያ በፕሪምየር ሉጉ አምና ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ በመጫወት አሳልፏል። ተጫዋቹ ዘንድሮ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ዝውውሩ ከመከፈቱ ከወራት በፊት ለሀዲያ ሆሳዕና ለመጫወት ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻም ምርጫውን ኢትዮጵያ ቡና አድርጓል።

አበበ በኢትዮጵያ ቡና የአራት ዓመት ውል የፈረመ ሲሆን ክለቡን የለቀቀው ፈቱዲን ጀማልን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!