ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መቐለ 70 እንደርታ የበርካታ ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን ተሳታፊው መቐለ 70 እንደርታ የ17 ነባር ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል፡፡

ባለፈው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ሕይወት አረፋይኔ እየተመሩ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት መቐለ 70 እንደርታዎች ለሁለተኛ ዓመት የሊጉ ተሳትፏቸው ተጠናክረው ለመቅረብ የተጫዋቾችን ውል ወደማደሱ ገብተዋል፡፡ አሰልጣኝ ህይወት አረፋይኔ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀችሁ ከሆነ የቡድኑን ጠንካራ ስብስብ ለማስቀጠል በማሰብ ውላቸው የተጠናቀቁ አስራ ሰባት ተጫዋቾች ለተጨማሪ ሁለት እና አንድ አመት ማራዘማቸውን ገልፀውልናል፡፡

ውላቸውን ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች- ፍሬወይኒ ገብሩ፣ ሸዊት አብርሃ

ተከላካዮች – ሊዲያ ልዑል፣ ሳምራዊት ኃይሉ፣ ፍሬወይኒ አበራ፣ ገነት ሀይሉ፣ ፍፁም ኪሮስ፣ ሰላም ለዓከ

አማካዮች – ፍሬወይኒ ገብረሚካኤል፣ ህይወት ኪሮስ፣ አበባ ገብረመድህን፣ ቅድስት ቦጋለ፣ ሰላም ተክላይ

አጥቂዎች – ዮርዳኖስ በርኸ፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ፣ አስካለ ገብረፃድቃን፣ ሳሮን ሰመረ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!