ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ጥበቡ ወርቁን ደግሞ በረዳት አሰልጣኝነት ተቀጥረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን በአሰልጣኝ አብዱራህማን ዑስማን እየተመሩ በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ተሳትፎቸውን ያደረጉት አቃቂ ቃሊቲዎች ከሳምንት በፊት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ባወጡት ማስታወቂያ መሠረት በዛሬው ዕለት አንደኛ በመሆን የቀድሞው የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና አሰልጣኝ እና በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ረዳት በመሆን የሠራው አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳ በዋና አሰልጣኝነት ሲቀጠር በምክትል አሰልጣኝነት ከተወዳደሩት መካከል በቼራሊያ ቡድን የሚታወቀው ጥበቡ ወርቁ ተቀጥሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!