ሁለት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥተዋል

አቃቂ ቃሊቲ እና ኢትዮጵያ መድን አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ማስታወቂያን አውጥተዋል፡፡

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ ጋር በመለያየት አዲስ የዋና አሰልጣኝ ቅጥር ማውጣቱን ሥራ አስኪየጁ አቶ ገዛኸኝ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። መስፈርቱን የሚያሟላ አሰልጣኝም ያለውን ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር እንደሚችልም ነግረውናል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ መድንም ከሰሞኑ ማስታወቂያ አውጥቶ አዳዲስ አሰልጣኞች ፍለጋ ላይ ተጠምዷል፡፡ በተሰረዘው የ2012 የከፍተኛ ሊግ ውድድር አጋማሽ ላይ አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን በማሰናበት አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን የቀጠረ ቢሆንም በወቅቱ ኮቪድ 19 በመግባቱ በጋራ ስምምነት በመለያየታቸው አዲስ ማስታወቂያን ክለቡ ሚውጣቱን ሰምተናል፡፡ ክለቡ ማስታወቂያ ካወጣ ሰንበትበት ያለ ሲሆን ከነገ በስቲያም የማወዳደር ሒደቱ ፍፃሜውን እንደሚያገኝ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!