ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ ዋና አሰልጣኝ ሾመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጀርመናዊ አሰልጣኝ መሾሙን ከደቂቃዎች በፊት በክለቡ ይፋዊ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ይፋ አድርጓል።

የክለቡ የሥራ አመራር ቦርድ አባል እና የማርኬቲንግ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት ውብሸት ከደቂቃዎች በፊት ይፋ እንዳረጉት ጀርመናዊው የ62 ዓመት አሰልጣኝ ኤርነስት ሚደንዶርፕ ጀረሰኞቹን ለሦስት ዓመታት ለመረከብ የተስማሙ ሲሆን ክለቡን ወደ ቀድሞ ውጤታማነት የመመለስ ግዴታ ተጥሎባቸው ሀላፊነቱን እንደተረከቡ ገልፀዋል። አክለውም ለዋና ሀላፊነት ቦታ ከ10 በላይ እጩዎችን አወዳድሮ ወደ ውሳኔ መብቃቱን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኙ የመጨረሻ ሥራቸው የነበረው በ2019/20 የደቡብ አፍሪካ የአብሳ ፕሪምየር ሺፕ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ የጨረሰው ካይዘር ቺፍስ ሲሆን ከዛ በፊትም በጋናው ኸርትስ ኦፍ ኦክን በመሰሉ ቡድኖች መሥራት ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከዚህ ቀደም በ1967 በፒተር ሸንግተር እና በ2005 በሚኬል ክሩገር ከተመሩ በኋላ ኤርነስት ሚደንዶርፕ ሦስተኛው ፈረሰኞቹን የመሩ ጀርመናዊ ይሆናሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!