ሰበታ ከተማ የመስመር ተከላካይ አስፈረመ

ሙሉቀን ደሳለኝ ሰበታ ከተማን ተቀላቀለ፡፡

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች በመሐል እና በመስመር ተከላካይነት መጫወት የሚችለው ሙሉቀን ደሳለኝን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረማቸውን ሥራ አስኪያጁ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በመከላከያ ረዘም ያሉ ዓመታትን ያሳለፈው ይህ ሁለገብ ተጫዋች በመስመር ተከላካይ ስፍራ ያለውን አማራጭ እንደሚያሰፋ ይጠበቃል።

አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር በሒደት ላይ ያሉት ሰበታዎች የቅጥር ማስታወቂያ ሜውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እስካሁን አምስት አሰልጣኞች ሲቪያቸውን ማስገባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!