ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሴናፍ ዋቁማ ማረፊያ ታውቋል

ሴናፍ ዋቁማ ለመከላከያ ለመጫወት ፊርማዋን አኑራለች፡፡
ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ የተገኘችውና ያለፉትን ሦስት ዓመታት በአዳማ ከተማ የነገሰችው ሴናፍ በ2011 ከአዳማ ከተማ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳች ሲሆን በዛኑ ዓመትም የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች ሆና ተሸልማለች፡፡

ውሏ ከአዳማ ጋር በክረምቱ የተጠናቀቀው ኮከቧ አጥቂ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሟ ሲያያዝ ቆይቶ ለአንድ ዓመት ለጦሩ ለመጫወት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝታ ፈርማለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!